News & Events

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. የጤናና ሕይወት ነክ ሽፋን ላላቸው ደንበኞቹ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ለሚመጡ ህልፈተ-ሕይወትም ሆነ ተያያዥ ወጪዎች ሽፋን እንደሚሰጥ አስታወቀ

  •      ኩባንያው ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሦስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል  

የኒያላ ኢንሹራንስ  ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ ሞላ በመንግሥት ለተቋቋመው የኮሮና ቫይረስ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሚያዝያ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ኩባንያው ያደረገውን የሶስት ሚሊዮን ብር ቼክ ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር ጥልቀትና ስፋት ቀድሞ በመረዳት በዚህ አስቸጋሪና ፈታኝ ወቅት ከክቡራን ደንበኞቹ ጎን መቆምና አለኝታነቱን  በተግባር ማረጋገጥ እንዳለበት በጽኑዕ ያምናል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ዋና ሥራ አስፈጻሚው እንዳሉት ምንም እንኳን ደንበኞች ቀደም ሲል የገዙት የጤናና ሕይወት ፖሊሲ በእንደዚህ ዓይነት ወረርሽኞች ለሚመጡ አደጋዎች ሽፋን የሚሰጥ ባይሆንም ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ከዓለም ዓቀፍ የጠለፋ ዋስትና ሰጪ ድርጅቶት ጋር በመነጋገር ከነባር ደንበኞቹ የካሳ ጥያቄ ቢቀርብ የሚያስተናግድ መሆኑን፤ በተጫማሪም ለአዳዲስ ደንበኞች ያለምንም ተጨማሪ የዐረቦን ክፍያ ሽፋን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው የወረርሽኙን ስርጨት በዋናነት ለመቀነስ በባለሞያዎች የተሰጠውን ማህበራዊ ፈቀቅታን (Social Distancing) ምክር ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ ለማዋል በማሰብ ደንበኞች የዋስትና ውሎችን ለማደስ፣ አዳዲስ ውሎችን ለመግዛት፣የካሳ ጥያቄ ለማቅረብ ወይም ማብራሪያ የሚሹበት ማንኛውም አይነት ጥያቄ ቢኖራቸው ወደ ቢሮ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ጥያቄዎቻቸውን የሚስተናገዱበት ሁኔታ ኩባንያው ያመቻቸ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->