News & Events

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ26 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዥ ፈጸመ

 
  • ኩባንያው እስከ ዛሬ በጠቅላላ  ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ የቦንድ ግዥ አከናውኗል፡፡

(ግንቦት  19 ቀን 2013 ዓ.ም፣ አ/አ)--የታላቁ  የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ለማፋጠን በሚደረገው ያላሰለሰ ጥረት  ለተከታታይ  አስር ዓመታት ሀገራዊ ድርሻውን ሲወጣ የቆየው ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. በዛሬው ዕለትም ለስምንተኛ ጊዜ ተጨማሪ የሃያ ስድስት ሚሊዮን 750 ሺህ ብር ቦንድ ግዢ በመፈጸም አጋርነቱን ሳይቷል፡፡

የ26 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዥ ርክክብ ሲካሄድ

የቦንድ ግዥው ሥነ-ሥርዓት ግንቦት  19 ቀን 2013  ዓ.ም የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ቦርድ አባላት  ከሆኑት መካከል አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፤ኢንጂነር ጌታሁን  ሁሴን፤   ክቡር አቶ ታደለ ይመር፤  የብሐራዊው ምክር ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታገል ቀኑብህ፤  የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ ሞላና የማኔጅመንት አባላት፤እንዲሁም በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎች  በተገኙበት በኢሊሊ  ኢንተርናሽናል ሆቴል ተከናውኗል፡፡

ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ቀደም ሲል  በሰባት ዙሮች  የ63 ነጥብ 25 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዥ በመፈጸም ለግድቡ ግንባታ መፋጠንና ስኬት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ችሏል፡፡ 

የዛሬውን  26  ሚሊዮን 750 ሺህ ብር ጨምሮ ኩባንያውእስከ አሁን ለግድቡ ግንባታ በጠቅላላ ከዘጠና  ሚሊዮን ብር በላይ  የቦንድ ግዥ ፈጽሟል፡፡

አቶ ያሬድ ሞላ የታላቁ  ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመላው ኢትዮጵያውያን የአንድነትና የአይበገሬነት የጋራ አሻራ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት መንግሥት የሁለተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት ሥራ ለማስጀመር ፍተኛ ርብርብ እያደረገ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ  ምዕራፍ ላይ ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ለስምንተኛ ጊዜ የቦንድ ግዥ ማከናወኑ ትልቅ ደስታ እንደሚሰማው ገልጸው የዛሬው ቦንድ ግዥ ለሦስተኛው ዙር የውኃ ሙሌት ስንቅ ይሆናል ብለዋል፡፡ 

ከተመሰረተ  ሩብ ክፍለ-ዘመን  ያስቆጠረው ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ.  ከመደበኛው የኢንሹራንስ ሽፋን መስጠት አገልግሎቱ በተጓኝ ሀገራዊ ኃላፈነቱን ለመወጣት በሚያስችለው መልኩ በርካታ ድጋፎችን ያደረገ ግዙፍና ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም ሲሆን በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ አንድ ዛፍ ለአንድ ደንበኛ “በሚልሰፊ ፕሮጀክት ቀርጾ ከሰላሳ ሺህ በላይ ችግኛችን በመትከልና በመንከባከብ በሀገሪቱ በሚካሄደው የአረንጓዴ ልማት መርሐ-ግብር ላይ የራሱን ትልቅ አሻራ በማሳረፍ ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው በየጊዜው ፍላጎትና ዕርካታን መሠረት ያደረጉ ጥናቶችን  በማድረግ አዳዲስ የኢንሹራንስ ሽፋኖችን በማቅረብ ለደንበኞቹ የአዕምሮ ሰላም (Peace of Mind) በመስጠት ላይ ሲሆን ይህንኑም ተከትሎ  በቅርቡ ለ-ሞባይሌየተሰኘ ልዩ የኢንሹራንስ ሽፋን በማቅረብ የስማርትፎን ተጠቃሚ ደንበኞች በቀን ከአንድ ብር እስከ አንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም ዐረቦን በመክፈል ስልካቸው ቢበላሽ፤ ቢሰረቅ ወይም ቢሰረቅ የካሳ ክፍያ የሚያገኙበትን ሁኔታ አመቻችቶ እየሠራ ይገኛል፡፡

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->