News & Events

የኒያላ ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ያሬድ ሞላ የመላው አፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት (African Insurance Organization) ዋና ፕሬዚደንት አድርጎ ሾመ

 

መቀመጫውን በካሜሩን ዋና ከተማ ያውንዴ ያደረገው የመላው አፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት (African Insurance Organization (AIO) ሰሞኑን 51ኛውን ኮንፈርንስና ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል  “የአፍሪካ ሀገራት የዕዳ ጫና በኢንሹራንስ ኩባያዎች ላይ በሚያደርሰው ጉዳትና የማቃኛ መንገዶች” በሚል ርዕስ  ሲያካሂድ ሰንብቶ የመዝጊያውን ሥነ-ሥርዓት ደግሞ እጅግ በደመቀ ሁኔታ  በሸራተን አዲስ በአከናወነበት ወቅት ደርጅቱን በከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት እንዲመሩ  አቶ ያሬድ ሞላን ዋና ፕሬዚደንት አድርጎ ሾሟል፡፡

አቶ ያሬድ ሞላ  በአሁኑ ጊዜ የኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ማህበር (Association of Ethiopian Insurers-AEI) ፕሬዚደንት ሆነው በማገልገል ላይ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በናሚቢያርዕሰመዲናዊንድሆክ በተካሄደው 50ኛው የድርጀቱ ኮንፈረንስና ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተመርጠው ድርጅቱን በምክትል ፕሬዚደንት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡

አቶ ያሬድ ሞላ ከናሚቢያዊቷ ሚስ ፓቲ ካሩዋይህ ማርቲን የፕሬዚዳንትነት ኃላፊነታቸውን በተረከቡበት  ወቅት እንደተናገሩት የመላው አፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ለዚህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ስለመረጣቸው ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው በድርጅቱ ውስጥ በሚኖራቸው የቆይታ ጊዜ በትጋትና በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ፤ በተለይም የአፍሪካ ሀገራት በኢንሹራንሱ ዘርፍ ያላቸው ዕድገት ከዓለም ሀገራት ጋር ሲነጻጸር  እጅግ ደካማ በመሆኑ ይህን ታሪክ ለመቀየር የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት እንደሚጥሩ ቃል ገብተዋል፡፡

በተለይም አቶ ያሬድ በፕሬዚዳነትነት ዘመናቸው በሚከተሉት ሶስት ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡

1ኛ፤ ኢንሹራንስ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ እንዲሆንና በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ ያለው አስተዋጽኦ የጎላ እንዲሆን፤ በተለይም ኢንሹራንስ በሚገባ ባልተዳረሰባቸውና አነስተኛ ገቢ ባላቸው የህብረተሰብ ክፍል ላይ አህጉሩ ትኩረት እንዲያደርግ፤

2ኛ. የኢንሹራንስ ሬጉሌሽንና የኢንሹራንስ ሙያና ባለሙያ የማሳደግና የማጠናከር ሥራ፤

3ኘ፤ ኢንሹራንስን ያማካለ ፈጠራና ዲጂታል ትራንስፎርሜሸንን ማሳደግና ማስፋፋት፤

አቶ አቶያሬድ በ2019 ዓ. ም (እንደአውሮፓውያን አቆጣጠር) በመላው አፍሪካ ከሚገኙ የኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር ተወዳድረው ባሳዩት ብቃት ያለው አመራር የዓመቱ ምርጥ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተብለው መሸለማቸው ይታወሳል ::

በአሁኑ ወቅት አቶ ያሬድ  በፈረንሳይParis School of Business የዶክትሬት ዲግሪ የሚያስገኘውን  ትምህርታቸውን  በማጠናቅ ላይሲሆኑበኢንሹራንስኢንደስትሪውላይምከ30 ዓመታትበላይየካበተልምድአላቸው::

አቶ ያሬድ በስትራተጂክ የሥራ አመራር (strategic leadership)፣ በሥጋት አመራር (Risk Management)፤ በገበያ ልማት (Marketing Development) ከፍተኛ ብቃትና ጥበብ ያላቸው በሳል መሪ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንደስትሪን ለማዘመን፤ ብቃት ያለው የኢንሹራንስ ባለሙያ እንዲኖር፤ በተለይም ኢንደስትሪው ራሱን ችሎ እንዲመራ የሚመለከታቸውን አካላት ሁሉ በማግበባት፤ የማህበረሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ የኢንሹራንስ አገልግሎቶች እንዲስፋፉ ለማድረግ በቁርጠኝነት የሚሰሩ ባለራዕይ መሪ ናቸው፡፡ 

በአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት የ53 ዓመታት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ93 ሀገራት ቁጥራቸው ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጋ  ከመላው አፍሪካ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ፤ ከአውሮፓና ከሌሎች ዓለማት የመጡ የኢንሹራንስ ባለሙያዎች፤ የፋይናንሺያል ኢንደስትሪ ኤክስፐርቶች፤ ፖሊሲ አውጪዎች፤ የቴክኖሎጂ አጋሮችና ኢንሹርቴኮች የተሳተፉ ሲሆን በኢንሹራንስ ዘርፍ የተደረጉ ጥናቶችና የምርምር ውጤቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1972 ዓ.ም የተመሠረተ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም ሲሆን ዋና ግቡም በመላው አፍሪካ የኢንሹራንስ ኢንደስትሪው በውድድር ላይ የተመሠረተ ጤናማ ዕድገት እንዲያስመዘግብ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው ::

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->