News & Events

የባለአክሲዮኖች 30ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 23ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

[Download pdf]

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1) ፣ 367(2) እና አንቀጽ 370 መሠረት የኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የባለአክሲዮኖች 30ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 23ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጥዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ሆቴል ሰሜን የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳሉ፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤዎቹ ላይ እንድትገኙልን የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

1. ማህበሩን የሚመለከቱ ወና ዋና መረጃዎች
 
1.1 የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ ----- አ.አ. ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 04፣ የቤ.ቁ.330፣ ስልክ +251116626667፣ ኢሜል nisco@ethionet.et ድረ-ገጽ www.nyalainsurancesc.com
1.2 የአክሲዮን ማህበሩ የንግድ ዘርፍ --------------------------- ኢንሹራንስ
1.3 የአክሲዮን ማህበሩ የንግድ ምዝገባ ቁጥር ----------------- BL/AA/3/0017533/2011
1.4 የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ---- ብር 1,733,726,000.00
1.5 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል) ------ ብር 1,095,451,502.00
 
2. የ30ኛው የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
 
2.1 ምልዓተ-ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
2.2 እስከ ጉባዔው ቀን የተፈጸሙትን የአክሲዮን ሽያጮችን እና ዝውውሮችን ማጽደቅና አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፣
2.3 የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ. የ2023/24 የሥራ ክንውን ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
2.4 እ.ኤ.አ. የ2023/24 የሥራ ዘመን የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማድመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
2.5 እ.ኤ.አ. የ2023/24 የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል በዳይሬክተሮች ቦርድ በቀረበ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
2.6 እ.ኤ.አ. ለ2024/25 የሥራ ዘመን የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና አበላቸውን መወሰን፤
2.7 ለቦርድ አባላት ወርሃዊ አበልና ከተጣራ የትርፍ ድርሻ የሚታሰብ ክፍያን መወሰን፤
2.8 የቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፣
2.9 የቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን ወርሃዊ አበል እና የሥራ ዋጋ መወሠን
 
3. የ23ኛው የባለአክሲዮኖች አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
 
3.1 ምልዓተ-ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፤
3.2 የአክሲዮን ማህበሩን የተሻሻለ መመስረቻ ጽሁፍ ተወያይቶ ማጽደቅ
 
4. ማሳሰቢያ፡
 
4.1 በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካዮቻችሁ ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ወይም በንግድ ሕግ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባዔው ከመካሄዱ ከሦስት ቀን በፊት በኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ዋና መ/ቤት፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201 በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማህበሩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልተው በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ስለመሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
4.2 የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ (ቢጫ ካርድ) ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
 
የኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

An overview

Nyala Insurance Share Company (NISCO) was founded in July 1995 following the liberalization of the insurance business to the private sector in 1994 with the Licensing and Supervision of Insurance Business Proclamation No. 85/1994. Read more...

Investments

Apart from its major investments in real estates in the downtowns of Addis Ababa, Bahir Dar and Nazareth, Nyala Insurance selectively invests in various financial institutions like Dashen Bank, which have potentially high investment returns. Read more...

Links

Contact us

Protection House, Mickey Leland Street

Tel: +251-11-6626679/80/76

-->